MENESHAYE (መነሻዬ) ልጆች እየተዝናኑ ለነገ እድገታቸው የሚበጅ ስኬታማ የትምህርት ቤት ቆይታ እንዲኖራቸው እንዲሁም በሕይወታቸው ውስጥ ብቁና የተሻሉ ሆነው እንዲገኙ የሚያግዛቸውን ትምህርታዊ መጫወቻዎች እና ለመማር ማስተማር አጋዥ የሚሆኑ ምርቶች ለገበያ የሚያቀርብ መለያ ስም ነው፡፡ 

ትምህርታዊ መጫዎቻዎቻችን በልጆች አእምሯዊ ልህቀት፤ አካላዊ እድገትና ማህበራዊ ግንኙነት ላይ አዎንታዊ ለውጥን በመፍጠር የልጆችን የመማር ሂደት የሚያነቃቁ ናቸው። በእነዚህ ትምህርታዊ መጫወቻዎች ልጆች ችግሮችን የመፍታት ክህሎታቸውን ማዳበር፤ የማሰላሰል አቅማቸውን መጨመር፤ የፈጠራ አቅማቸውን ማጎልበት፤ የተግባቦት ክህሎታቸውን ከፍ ማድረግ፤ በራስ መተማመናቸውን ማዳበርና ለነገሮች ትኩረት እንዲሰጡ ማስቻልን የመሳሰሉ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ያገኛሉ።

MENESHAYE (መነሻዬ) በራሱ አዘጋጅቶ ለገበያ የሚያቀርባቸው ለመማር ማስተማር አጋዥ የሚሆኑ ምርቶች ዓለም የደረሰበትን የማስተማሪያ ስልትና ቴክኖሎጂ በመውሰድ ለሀገራችን እንዲስማማ ተደርገው የሚቀርቡ ናቸው፡፡  እነዚህም የቋንቋ፣ የሂሳብ፣ የሳይንስ እና ሌሎችም ልጆች ሊያውቋቸው የሚገቡ ትምህርቶችን የሚያካትቱ ሲሆን ልጆችም ሳይሰላቹ ደስተኛ ሆነው እንዲማሩ ያስችላቸዋል።

የልጆችን መነሻ በማቅለል መንገዳቸውን ቀና መዳረሻቸውም ብሩህና ፍሬያማ እንዲሆን በማስቻል ብቁና የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎችን ማፍራትን አላማው አድርጎ ሁሌም በትጋት እንሰራለን።

ጉርድ ሾላ፤ ሆሊሲቲ ሴንተር 3ኛ ፎቅ

ፒያሳ፤ ካንትሪ ታወር 2ኛ ፎቅ

0989939393 |  0930323334

ይምጡ በመነሻዬ የልጅዎን መነሻ ያቅልሉ!